በጉራጌ ዞን ማንኛውንም ሰብሰባ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እና የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ የሚከለክል ገደብ ተጣለ

0
1048

ሐሙስ ነሐሴ 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በጉራጌ ዞን ማንኛውንም ሰብሰባ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እና የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ የሚከለክል አስቸኳይ ትዕዛዝ (ኮማንድ ፖስት) መተላለፉን የደቡብ ክልል ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።

ኮማንድ ፖስቱ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ መንግሥታዊ ስብሰባዎችም እንዳይካሄዱ ብሏል።

ከዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው በዚህ ክልከላ መሰረትም፤ የንግድ ሱቆችና ተቋማትን ያለምንም ምክንያት መዝጋትና ማንኛውም ሰልፍና መሰል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ ሲሆን የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃድ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት እስከ 2 ሰዓት ድረስ ብቻ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።

አዲስ ማለዳ ከወልቂጤ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባገኘችው መረጃ መሰረትም፤ የመንግስት ሠራተኞች በሥራ ሰዓት ቢሮ የመገኘት ግዳጅ የተጣለባቸዉ ሲሆን፤ የኮማንድ ፖስቱን ትዕዛዝ በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የደቡብ ክልል ኮማንድ ፖስት ማስታወቁ ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here