አዋሽ ባንክ በዘንድሮ በጀት አመት 5.58 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አስመዘገበ

0
453

አዋሽ ባንክ እ.አ.አ በ2020/2021 በጀት ዓመት ከአጠቃላይ ገቢው 5.58 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ባንኩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በተለይም በዘንድሮ የሂሳብ ዓመት ከተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ምንጮች ከ906 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘት መቻሉንም ባንኩ ገልጧል፡፡ በዚህም ረገድ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የውጭ ምንዛሬ ግኝቱ የ37 ሚሊዮን ዶላር ዕድገት ማሳየቱን አስታውሷል፡፡
በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ታሪክ ባንኩ ከአምስት አመት በፊት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ አስመዝግቦ ታሪክ መስራቱን አውስቶ፣ በዘንድሮው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 5.58 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አንስቷል፡፡ ይህም የባንኩ ገቢ አምና ከነበረበት 10.2 ቢሊዮን ወደ 13.7 ቢሊዮን ብር ማሳደግ በመቻሉ እንደሆነም በመግለጫው አመልክቷል፡፡
ለዚህም ትርፍ መገኘት እና ለተመዘገበው ስኬት ዋና ምክንያት ብሎ ባንኩ ያነሳው የዓለም ምጣኔ ሀብት (ECONOMY) ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ማገገሙ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማደግ እና ባንኩ የወሰዳቸው የተለያዩ የፖሊሲ እርምጃዎች ናቸው፡፡ መግለጫው አክሎም ባንኩ በተቀማጭ ሂሳብ፣ በብድር እና ትርፋማነት ብቻ ሳይሆን በተከፈለው የካፒታል መጠንም መሪነቱን ይዞ መቀጠሉን ጠቅሷል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 140 ሐምሌ 4 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here