መነሻ ገጽዜናአቦል ዜናበአዲስ አበባ መንግሥት ሕጋዊ ካርታ እያለን ንብረታችን ነጥቆናል ሲሉ ተበዳዮች ገለጹ

በአዲስ አበባ መንግሥት ሕጋዊ ካርታ እያለን ንብረታችን ነጥቆናል ሲሉ ተበዳዮች ገለጹ

በአዲስ አበባ የካ ከፍለ ከተማ ወረዳ10 በተለምዶ አንቆርጫ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከኹለት ዓመት በፊት ከባለ ይዞታዎች መሬት በውል ገዝተው የሰሩትን ቤት መንግሥት ለልማት ይፈለጋል በማለት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ቤታቸውን በዶዘር እንዳፈረሰባቸው ኗሪዎች ገለጹ።

ተበዳዮች ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ አንደገለጹት ከሆነ ከባለ ይዞታዎች በሕጋዊ ውል ተፈራርመው የገዙት ቦታቸውን ቦታው ለልማት ይፈለጋል በማለት መንግሥት የቤት ንበረታቸውን እንኳን ሳያወጡ ባለበት በዶዘር አፍርሶብናል ብለዋል።
ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ከገለጹት ተበዳዮች መካከል ደንኤል ቦንጃ አንዱ ናቸው። ዳንኤል በአዲስ አበባ የካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 10 አንቆርጫ አከባቢ ከኹለት ዓመት በፊት በሕጋዊ ውል ከመሬቱ ባለ ይዞታ በ375 ሺሕ ብር የገዙት 200 ካሬ ቦታቸውን በማያውቁት ሁኔታ እንዳጡ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ዳንኤል የስምንት ቤተሰብ አስተዳዳሪ ሲሆኑ፣ ቤተሰባቸውን የሚስተዳድሩት በጥበቃ ተቀጥረው በሚገኙት የወር ገቢ ነው። ይሁን አንጅ ዳንኤል ድንገት ቤታቸው መፍረሱንና የቤት ንበረታቸው ባለበት መቅረቱን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸውን ቤት ተከራይተው ማኖር አልቻሉም። በመሆኑም የዳንኤል ቤተሰብ ቤታቸው በድንገት ከፈረሰ ብኅላ የገጠማቸው እጣ ፈንታ ሸራ ቤት ወጥሮ መኖር መሆኑን ዳንኤል በምሬት ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ደንኤል ሁኔታውን ለአዲስ ማለዳ ሲስታውሱ “ደንገት ቤቴ ከነንብረቴ ሲፈርስብኝ የምሄድበት ግራ ገባኝ፣ ይሄን ችግሬን ያየ በአከባቢው የሚኖር ደግ ሰው በሱ ቦታ ላይ ሸራ ወጥሬ ቤተሰቤን እንዳስጠልል ፈቅዶልኝ አሁን ከነ ቤተሰቤ የምኖረው በሸራ ቤት ነው።” ሲሉ ገልጸውታል።

ከኪራይ ቤት ተላቅቄ እረፍት አገኛለሁ ብለው ከወዳጅ ዘመዳቸው ገንዘብ አሰባስበው የሰሩትን ቤታቸውን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማጣታቸወን የሚስታውሱት ዳንኤል፣ መንግሥት እንደ ዜጋ ከቆጠረን መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ተማጽነዋል።
ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ ያሳሰቡ ተበዳይ በተመሳሳይ ጊዜ ቦታ ገዝተው የሰሩት ሶስተ ጓደኞቻቸውና የራሳቸው ቤት እንደፈረሰባቸው ተናገረዋል። ቤታቸውን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዳጡ የሚናገሩት ተበዳዮቹ መሬቱን የሸጡላቸው ባለይዞታቾች መንግሥት ቤታቸውን ሲፈርሰው በሕጋዊ ውል የሸጡት መሆኑን ለበማስረዳት ሊግዟቸው እንዳልቻሉ ነው ተበዳዮች የገለጹት።

አዲስ ማለዳ በአከባቢው ቤታቸው ከፈረሰባቸው ሰዎች እንደሰማችው ከሆነ ከባለ ይዞታዎች መሬት የገዙበት የውልና ማስረጃ ወረቀት በእጃቸው ይገኛል። ከባለ ይዞታዎች ቦታ ቦታው ለልማት ተፈልጓል ተብሎ በመንግሥት ቢነሳም ምንም አይነት የተሰጣቸው ካሳም ይሁን ቦታ እንደሌለ ነው ለአዲስ ማለዳ የገለጹት።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ተበዳዮች እንደገለጹት ከሆነ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ግምት ከ100 በላይ እንደሚሆን ይገመታል።
በጉዳዩ ላይ ምላሹን ለአዲስ ማለዳ የሰጠው የየካ ከፍለ ከተማ ቅሬታ አቅራቢዎች ቅሬታቸውን ለከተማ አስተዳደሩም ይሁንለክፍለ ከተማው አቅርበው ሕጋዊ ማረጃ ካላቸው ቅሬታቸቸው ይፈታል ብሏል። አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሸገር ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ ለልማት የተለዩ ቦታዎችን እየለካና እያጠረ መሆኑን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ ሁናቸው ጌትነት ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቅሬታቸው ሕጋዊ ተገቢነት ያለው ከሆነ ለከተማ አስተዳደሩ አቅርበው ካሳ የሚገባቸው ከሆነ ካሳ ሊገኙ ይችላሉ ነው ያሉት ሁናቸው። ይሁን እንጅ ውልና ማስረጃ ስላላቸው ብቻ ካሳ ያገኛሉ ማለት አይቻልም ብለዋል ሁናቸው።


ቅጽ 2 ቁጥር 124 መጋቢት 11 2013

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች