የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በሦስት ተጨማሪ ቋንቋዎች ሥርጭት ሊጀምር ነው

0
856

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ባስገነባው ስቱዲዮ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ በትግረኛ፣በኦሮምኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑንም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሙሉቀን ሰጥየ ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።

 

አዲስ አበባ አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው የአማራ ልማት ማዕከል (አልማ) ህንጻ ላይ ባስገነባው ስቱዲዮ የቀጥታ ስርጭት መጀመሩንም በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ቀደም ድርጅቱ በአዲስ አበባ የሚሰራቸውን ዜናና ፕሮግራሞችን ለማሰራጨት ወደ ባህርዳር  ወና መሥሪያ ቤት ይልል የነበረ  ሲሆን  ከአሁን በኋላ ግን አዲስ አበባ በሚገኘው እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ባደራጀው የማሰራጫ ስቱዲዮው ሥራውን እንደሚያካሂድ  የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የስቱዲዮ ግንባታ ሥራውን ለማጠናቀቅ ስድስት ወራት እንደፈጀ የገለጹት ሙሉቀን፤ ለግንባታው የወጣው አጠቃላይ ወጪ ግን ይፋ አላደረጉም።

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here