መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናየዓለም ባንክ ለ4 የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት አዲስ ዳይሬክተር ሾመ

የዓለም ባንክ ለ4 የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት አዲስ ዳይሬክተር ሾመ

የዓለም ባንክ አቶ ኬት ሃንሰንን የኬንያ፣ ርዋንዳ፣ ሶማሊያ እና ኡጋንዳ ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ፡፡
ልማትን የተመለከቱ የ30 ዓመታት ልምድ ያላቸው ሃንሰን የ13 ቢሊዬን ዶላር ዋጋ ያላቸው እና በ4ቱ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የተሚተገበሩ 100 ፕሮጄክቶችን ይመራሉ ተብሏል፡፡
ትኩረታቸው በኮሮና ወረርሽኝ ላይ አድርገው ሃገራቱ የጀመሩትን የዘላቂ ልማት ጉዞ እንደሚደግፉም ነው የተገለጸው፡፡
ከአሁን ቀደም አፍሪካን ጨምሮ ደቡብ አሜሪካን በመሳሰሉ የተለያዩ ክፍለ አህጉራት በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት ሃንሰን የባንኩ የሰብዓዊ ልማቶች ምክትል ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉም ሲሆን ዋና ስራ አስፈጻሚውን ያማክሩም እንደነበር የህይወትና የስራ ልምድ ማስረጃዎቻቸው ያሳያሉ፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 97 መስከረም 2 2012

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች