የትራንፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በተለያዩ የትራንፖርት አገልግሎት መስጫ መናኸሪያዎች በመዘዋወር ጉብኝት አደረጉ

0
1388

የትራንፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከለላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመናኸሪያዎች አገልግሎት አሰጣጥን እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎቱ ተገልጋዮች፣ ሹፌሮችና ሌሎች የአገልግሎቱ ባለድርሻ አካላት በማድረግ ላይ የሚገኙትን ጥንቃቄ ዛሬ ማለዳ ጎብኝተዋል፡፡

ሚንስትሯ የአስኮ፣ የመርካቶና የአየር ጤና መናኸሪያዎችን የአገልግሎት አሰጣጥና ቫይረሱን ለመከላከል በማድረግ ላይ የሚገኙትን ጥንቃቄ ተመልክተዋል፤ የአገልግሎቱን ተጠቃሚ ተሳፋሪዎችን እንዲሁም በመናኸሪያዎቹ አገልግሎት የሚሰጡትን ሹፌሮችም አነጋግረዋል፡፡

በአገሪቱም የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል በህዝብ መገልገያ ትራንስፖርቶች ውስጥ እየተደረገ ያለውን ጥንቃቄና የኬሚካል ርጭት በመዘዋወር ተመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በየመናህሪያዎቹ ሚኒሚዲያዎች የጥንቃቄ መልዕክቶች እየተላለፉ መሆኑንና በተለያዩ በራሪ ወረቀቶችና ባነሮች ላይ መልእክቶችን በማዘጋጀት ለመንገደኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተከናወኑ እንዳሉም መመልከት መቻላቸው ታውቋል፡፡

ሚኒስትሯ የኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሁሉም መናኸሪያዎች የበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥሉ ይገባል ያሉ ሲሆን የክልል መናኸሪያዎችም በተመሳሳይ ቫይረሱን ለመከላከል ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here