መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናበአሜሪካ የዴሞክራት 117ኛው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ...

በአሜሪካ የዴሞክራት 117ኛው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ህጎች ሙሉ ለሙሉ መሰረዛቸው ተገለጸ

ሐሙስ ጥር 4 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአሜሪካ የዴሞክራት 117ኛው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ የጣለው ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ህጎች፣ ወጥተው የነበሩት ህጎችና እና ረቂቅ ህጎች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸውን የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት አስታወቀ።

አዲሱ የሪፐብሊካን 118ኛው ምክርቤት ኮንግረሱን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠሩ የዲሞክራቶች ረቂቅ ህጎች ሙሉ በሙሉ ጊዜው ያለፈባቸው ሆነዋል ተብሏል።

የካውንስሉ ሰብሳቢ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ፣ ይህ እንዲዘገይ ለሰራችሁ የካውንስሉ አባላትና ዩኒቲ ፎር ኢትዮጵያ ትልቅ ምስጋና አለን ብለዋል።ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ጉዳይ ከድጡ ወደ ማጡ በመሆኑ፣ በዜጎች ላይ እየተከሰተ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ከአዲሱ የኮንግረሱ መሪ ኬቨን ማካርቲ ኃላፊዎች ጋር ንግግር መጀመሩን ምክር ቤቱ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ገልጿል።

በተያያዘ ዜና፤ የኢትዮጵያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል፣ ለከፍተኛ ስብሰባ ከእስራኤል ባለስልጣናት በወቅቱ ጉዳይ ጋር ለመወያየት ልዩ የልኡካን ቡድን ዛሬ ከአሜሪካ ተነስቶ ወደ እስራኤል የሚገባ መሆኑን ተጠቁሟል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች