ዳሸን ባንክ ከሜክሲኮ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፎቶ ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ

0
760

የፎቶ ኤግዚቢሽኑ እስከ ታህሳስ 15 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል

ሐሙስ ኀዳር 8 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ዳሸን ባንክ ሜክሲኮና ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 73ተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከሜክሲኮ ኤንባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፎቶ ኤግዚቢሽን (አውደ ርዕይ) በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በይፋ ተከፍቷል፡፡

በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ የዳሽን ባንክ ከፍተኛ አመራሮች፣ የንጉሰ ነገስት ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ቤተሰቦች፣ በኢትዮጵያ የሜክሲኮ ኤንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ከ100 በላይ የሚሆኑ አገራት አምባሳደሮች፣ ቆንስላዎች፣ ተወካዮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡በፎቶ ኤግዚቢሽኑ ላይ ኢትዮጵያና ሜክሲኮ ያላቸውን ዘርፈ ብዙ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያሳዩ በርካታ ፎቶ ግራፎች ለዕይታ ቀርበውበታል፡፡

 

ኢትዮጵያና ሜክሲኮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ኢትዮጵያ በጣሊያን ዳግም በተወረረችበት ወቅት ሜክሲኮ ወረራውን በመቃወም ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟን ተከትሎ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በ1954 ሜክሲኮን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ነበር፡፡

በወቅቱ በሜክሲኮ በኢትዮጵያ ሥም አደባባይ የተሰየመ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም በሜክሲኮ ሥም አደባባይ በአዲስ አበባ በመሰየም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን መጀመራቸው ይታወቃል፡፡

በዛሬው ዕለት በይፋ የተከፈተው የፎቶ ኤግዚቢሽም ይህንኑ የኹለቱን አገራት ቀደምት ወዳጅነት የማጠናከርና የህዝብ የህዝብ ግንኙነቱን የማጎልበት አላማን ያነገበ ሲሆን፤ ኤግዚቢሽኑ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2015 ድረስ ለተመልካች ክፍት እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here