መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናየዓለም አቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ መክፈት የሚያስችለውን...

የዓለም አቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ መክፈት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

የዓለም ዐቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ መክፈት የሚያስችለውን ስምምነቱን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የዓለም ዐቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ተፈራርመዋል።

ይህም በትምህርት ልማት የሚደረገውን ጥረትና ከዓለም ዐቀፍ ተቋማት ጋር የሚደረገውን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ የዚህ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ መከፈቱ ትብብሩን ያሳድገዋል ነው የተባለው።

የዚህ ተቋም መሥሪያ ቤት በኢትዮጵያ መከፈት በትምህርት ዘርፍ ያሉትን አማራጭ አቅሞች ለመጠቀም እንደሚያስችል ተመላክቷል።

የዓለምማቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት በበኩሉ፣ ኹለንተናዊ ሰብአዊነትና ተራማጅ ማኅበራዊ ፖሊሲዎችና በሥርአተ ትምህርት፣ ይዘትና ትምህርት ውስጥ ዘላለማዊ አዲስነት ለመፍጠር ድርጅቱ በኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤቱን መክፈቱ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብሏል።

ድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ መክፈቱ ኢትዮጵያ በትምህርት እድገት ተደራሽነትና ጥራት የምታደርገውን ጥረት ያግዛል የሚል እምነት ተጥሎበታል።


ቅጽ 5 ቁጥር 209 ጥቅምት 26 2015

 

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች