የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 2.2 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የአገር ውስጥ ግብዓቶችን እንዲሁም 18. 9 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ግብዓቶችን ከውጭ በማስገባት ለተጠቃሚዎች የሚያቀርብ መሆኑን አስታወቀ።
በዘርፉ የሚታየውን እጥረት ለመቅረፍ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ከውጭ እና ከአገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ እንደሆነ የገለጹት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሺእመቤት ነጋሽ፣ ባለፈው ዓመትም ግምቱ 19 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ዘይት ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ መደረጉን ተናግረዋል።
ድርጅቱ መንግሥታዊ እንደመሆኑ መጠን ትርፉን ከማሳደግ ይልቅ ኅብረተሰቡን በማገልገል ላይ ያተኮረ ነው ያሉት የሺእመቤት፣ ይህንን እቅድ ለማሳካት ያመች ዘንድ የሥራ ካፒታልን በማሳደግ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን የማቅረብ አቅምን ከፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር ውይይት እንደተደረገ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በመላ አገሪቱ ባሉት 83 ቅርንጫፎች እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ቅጽ 5 ቁጥር 209 ጥቅምት 26 2015