የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በተያዘው ዓመት የስንዴ ምርትን በዘመናዊ ግብይት ሥርዓት ለማገበያየት መዘጋጀቱን አስታውቋል።
የስንዴ ምርትን በዘመናዊ የግብይት ሥርዓት መምራት የሚያስችል ዝግጅት የተደረገ በመሆኑ በተያዘው ዓመት ተቋሙ ማገበያየት እንደሚጀምር ነው የተገለጸው፡፡
ምርት ገበያው ስንዴን በዘመናዊ ግብይት ሥርዓት ማገበያየት የሚያስችለውን ረቂቅ ውል ያዘጋጀ ሲሆን፣ ውሉን በማፅደቅ በዚህ ዓመት ማገበያየት እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡
ምርት ገበያው ባሉት 25 ቅርንጫፎች አብዛኞቹ ከፍተኛ ስንዴ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ በመሆኑ አርሶ አደሩና አቅራቢው በቀላሉ ምርቱን ማስረከብ እንደሚችሉም ነው የተመላከተው፡፡
በተጨማሪም አርሶ አደሩና አቅራቢው ምርቱን ወደ ምርት ገበያ ሲያመጣ ተፈትሾ ደረጃ ከተሰጠው በኋላ፣ የአጭር ጊዜ ብድር ማግኘት የሚያስችለውን የመጋዘን ደረሰኝ በመቀበል የብድር አገልግሎት የሚያስገኝ ሥርዓት መዘርጋቱም ተጠቁሟል።
በተመሳሳይም ምርት ገበያው የእጣን፣ ኮረሪማ፣ ሩዝና የግብጦ ምርቶችን በዚህ ዓመት ማገበያየት እንደሚጀምር ነው የተገለጸው።
ቅጽ 4 ቁጥር 208 ጥቅምት 19 2015