መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናበክፍያ መንገዶች ላይ ከጥቅምት 22 ጀምሮ የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚደረግ ተነገረ

በክፍያ መንገዶች ላይ ከጥቅምት 22 ጀምሮ የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚደረግ ተነገረ

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በክፍያ መንገዶች ላይ ከጥቅምት 22/2015 ጀምሮ አዲስ የክፍያ ታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ኢንተርፕራይዙ ላለፉት ስምንት ዓመታት ቀልጣፋና ዘመናዊ በሆነ መልኩ ያልተቋረጠ የክፍያ መንገድ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፤ የአገራችን ዋነኛ የወጪ እና ገቢ ንግድ መስመር የሆነውን የአዲስ አበባ – አዳማ፣ በጅቡቲ መስመር ምሥራቃዊ የአገራችንን ክፍል የሚገኘውን የድሬደዋ – ደወሌ እንዲሁም የምሥራቅ አፍሪካ የትራንስ ሀይ-ዌይ መንገድ አያያዥ የሆነውን የሞጆ – ባቱ የፈጣንና የክፍያ መንገዶችን ተረክቦ በማስተዳደር ላይ ይገኛል።

መንገዶቹ የገቢ-ወጪ ንግድ ኮሪደር አካል እንደመሆናቸው የሎጂስቲክ ሥርአቱን ውጤታማነትን በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ፋይዳቸው የጎላ ነው ያለው ኢንተርፕራይዙ፣ ለሚሰጠው አገልግሎት ተመጣጣኝ የክፍያ ታሪፍ መተግበሩ ለአገልግሎቱ አዋጭነት እና ዘላቂነት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ገልጿል።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የፈጣን የክፍያ መንገድ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ እሳቤ ተሽከርካሪዎች የፍጥነት መንገድን ሲጠቀሙ ከሚያገኙት የጉዞ ጊዜ ቅናሽ፣ የነዳጅ ወጪ ቅናሽ ሌሎች የተሽከርካሪ ማንቀሳቀሻ ወጭዎች ቅናሽ እንዲሁም ከመንገዱ ዘመናዊነት ጋር ተያይዞ በፍጥነት መንገዱ ላይ ማሽከርከር ከፍተኛ የሆነ ምቾት እና የደኅንነት ጥቅም ማግኘታቸው የሚጠቀሱ ናቸው ብሏል።

በመሆኑም የታሪፍ ማሻሻያው ደንበኞች ከፍጥነት መንገዶቹ የሚያገኙትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲሁም የኦፕሬሽን እና የመንገድ ሀብት ጥገና ወጪ እድገትን ታሳቢ ያደረገ እና ተቋማዊ የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግ የታለመ መሆኑ ተገልጿል።

ታሪፉ ተሽከርካሪዎች በተጓዙት ርዝመት እና በአራት የክፍያ መደቦች ተከፍለው (አነስተኛ ተሽከርካሪዎች፣ መለስተኛ ተሽከርካሪዎች፣ የጭነት ተሽከርካሪዎች፣ ከባድና ተሳቢ ተሽከርካሪዎች) እንደሚከፍሉም ተነግሯል።


ቅጽ 4 ቁጥር 208 ጥቅምት 19 2015

 

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች