ምንጭ፡-Global Climate Risk Index (2021)
በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአገራት ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ የሚያጠናው ተቋም ይፋ እንዳደረገው፣ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከፍተኛ ጉዳት ካስተናገዱ አገራት መካከል ሞዛምቢክ፣ ዙምባቡዌና ባሀማስ ቀዳሚዎች ናቸው።
ሞዛምቢክ ካላት አጠቃላይ የኢኮኖሚ መጠን 12 በመቶ በላይ የሚሆነውን በዚሁ ችግር አጥታለች።
ጠንካራ ኢኮኖሚ እንዳላት የሚነገርላት ጃፓንም የጉዳቱ ሰለባ ተብላ በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
በአየር ንብረት ለውጥ ክፉኛ ተጎድተዋል ተብለው ከተዘረዘሩ አስር አገራት አብዛኞቹ ከአፍሪካና ከእስያ ናቸው።
ከእነዚህም አምስቱ አገራት ከአፍሪካ ሲሆኑ፣ ሶስቱ ከእስያ አህጉር ናቸው።
በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ዓለም ከፍተኛ ቀውስ እያስተናገደች መሆኑ ይታወቃል።
ቅጽ 4 ቁጥር 207 ጥቅምት 12 2015