መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናየዶሮና የእንስሳት ሀብት አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የዶሮና የእንስሳት ሀብት አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ፕራና ኢቨንትስ ከሱዳኑ ኤክስፖ ቲም ጋር በመተባበር ለሦስት ቀናት የሚዘልቅ የእንስሳት ሀብት አውደ ርዕይ ከጥቅምት 17 እስከ 19/2015 በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

በአውደ ርዕዩ ላይ ከ10 አገራት የተውጣጡ ከ70 በላይ ኩባንያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከ4 ሺሕ በላይ የዘርፉ የንግድ ባለድርሻዎች እንዲሁም ባለሙያዎችም የንግድ ግንኙነት ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አውደርዕዩ በግብርና ሚኒስቴር የሚደገፍና በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ ልማት ድርጅት የኢትዮጵያ እንስሳት ልማት ማኅበር፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎችና አቀነባባሪዎች ማኅበር አጋሮቹ ናቸው።

መንግሥት በ10 ዓመት የልማት እቅዱ የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ማሳየቱን የገለጹት የአውደ ርዕዩ አዘጋጆች፣ መሰል ዝግጅቶች የመንግሥት እቅድ እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

የዶሮ ኤክስፖው ለ11ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን፣ የእንስሳት አውደርዕዩ ደግሞ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄድ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።


ቅጽ 4 ቁጥር 207 ጥቅምት 12 2015

 

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች