መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናየአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክትን ወደ ሥራ ለማስገባት እንቅስቃሴ ተጀመረ

የአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክትን ወደ ሥራ ለማስገባት እንቅስቃሴ ተጀመረ

በጦርነቱ ምክንያት ውድመት እና ዘረፋ የደረሰበትን እና ተቋርጦ የቆየውን የአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክትን ወደ ሥራ ለማስገባት እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

የባቡር መስመሩ በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ ፕሮጀክቱን እያከናወነ ያለው ተቋራጭ ለተበላሹ፣ ለተዘረፉት እና ለወደሙ ንብረቶቹ ካሳ መጠየቁን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።

ኮርፖሬሽኑ የተቋራጩን ጥያቄ ለመመለስ ብሎም አጠቃላይ የባቡር ሥራውን ለማስቀጠል ቅርንጫፎችን በመክፈት እና የጠፉ እና የወደሙ ንብረቶችን በመለየት በየአካባቢው ጥናት እያደረገ መሆኑን ነው ያስገነዘበው።

270 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የአዋሽ-ኮምቦልቻ የባቡር መስመር በጦርነቱ ወቅት በከፋ ሁኔታ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል። የአዋሽ-ኮምቦልቻ የባቡር መስመር 99 በመቶ ከ3 ዓመት በፊት ተጠናቆ የነበረ፣ ነገር ግን በኃይል እጥረት ምክንያት የዘገየ መሆኑም ተጠቅሷል።

እስካሁን በተደረገው ጥናት የአዋሽ-ኮምቦልቻ የባቡር መስመር ከፍተኛ ዘረፋ፣ ውድመት እና ጉዳት ደርሶበታል ነው የተባለው።

ፕሮጀክቱ ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ በጀት ተይዞለት የተሠራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ 50 በመቶ ተጠናቅቆ የነበረው ከወልዲያ መቀሌ የሚወስደው የባቡር መስመርም ጉዳት እንደደረሰበት ተጠቅሷል።

የደረሰውን ውድመት አስተካክሎ ወደ ሥራ እንዴት መግባት ይቻላል በሚለው ላይ ጥናቶችን በማካሄድ በየአካባቢው ያሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን እየከፈቱ ዳግም ሥራ ለማስጀመር በንግግር ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስገንዝቧል።


ቅጽ 4 ቁጥር 207 ጥቅምት 12 2015

 

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች