መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናህወሓት በአማራና በአፋር ክልሎች 3 ሺሕ 598 ንጹሃኖችን መግደልን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ...

ህወሓት በአማራና በአፋር ክልሎች 3 ሺሕ 598 ንጹሃኖችን መግደልን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸሙ ተጠቆመ

ማክሰኞ መስከረም 10 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድን በአማራና በአፋር ክልሎች ከህግ ውጪ 3 ሺሕ 598 ንጹሃን ሰዎችን መግደልን ጨምሮ በጦር ወንጀል የሚያስጠይቁ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸሙ ተጠቆመ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፅህፈት ቤት የጋራ ምርመራ ዉጤቶችን ተከትሎ በኢትዮጵያ መንግስት የተቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረ ሃይል የምርመራና ክስ ኮሚቴ የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲያጣራ መቆየቱ ይታወቃል።

የግብረ ሃይሉ የምርመራና ክስ ኮሚቴ በአፋርና አማራ ክልሎች በሚገኙ ዘጠኝ አካባቢዎች የተፈጸሙ ጥፋቶችን የምርመራ ውጤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ሪፖርቱን ረቂቅ አውጥቷል።

በዚህም በወልዲያ፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ጃማ ወረኢሉ፣ ደሴና ኮምቦልቻ አካባቢዎች እንዲሁም፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን እና በአፋር ክልል እ.አ.አ ከመስከረም 15 ቀን 2021 እስከ ጥር 31/2022 ድረስ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አጣርቷል።

የምርመራና ክስ ኮሚቴው ባደረገው ማጣራት፤ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ ህግ የጣሱ በጦር ወንጀል የሚያስጠይቁ በርካታ ጥፋቶችን የህወሓት እና የሸኔ ቡድኖች መፈጸማቸውን ማረጋገጡን ገልጿል።

በዚህም ከህግ ውጪ 3 ሺሕ 598 ሰዎች ተገለዋል፣ 1 ሺህ 315 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ 2 ሺሕ 212 ሰዎች የአስገድዶ መድፈርና ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል እንዲሁም 452 ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸው ተነክቷል ሲል ሪፖርቱ አመላክቷል።ይህ አሰቃቂ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በህወሓት እና ሸኔ አማካኝነት መፈጸማቸውን ገልጿል።

ከህግ ውጪ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ ሪፖርቱ እንዳመለከተው በወልዲያና አካባቢው ብቻ 1 ሺሕ 181 ሰዎች በህወሓት ግድያ የተፈጸመባቸው መሆኑን ገልጿል።

በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ህወሓትና ሸኔ በፈጸሙት ግድያ በሰሜን ሸዋ ዞን 257 ሰዎች እንዲሁም በኦሮሞ ብሔረሰብ 162 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአፋር ክልል ከፍተኛ ጥፋት ያደረሰው የህወሓት ቡድን የ263 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉንም ሪፖርቱ አመላክቷል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች