መነሻ ገጽማረፊያ10ቱ10 የሴቶች ብዛት ከወንዶች የሚበልጥበት አገራት

10 የሴቶች ብዛት ከወንዶች የሚበልጥበት አገራት

ምንጭ፡-ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው (2022)

ወርልድ አትላስ የዓለም ባንክን ዘገባ ዋቢ አድርጎ እንዳሰፈረው ከሆነ፣ በዓለማችን ኔፓል ካላት ሕዝብ አንጻር በርካታ ሴቶች ያሉባት አገር ሆና ተመዝግባለች። ይህም በመቶኛ 54.4 ሲሆን፣ በቁጥር ሲቀመጥ በኔፓል 13 ሚሊዮን የሚሆኑት ወንዶች፤ 15.6 ሚሊዮን ደግሞ ሴቶች ናቸው ማለት ነው።

በዚህ የዐስርቱ ዝርዝር ውስጥ ከሕዝባቸው ቁጥር ውስጥ የሴቶች ብዛት ከወንዶች የሚበልጥባቸው አገራት አብዛኞቹ በአውሮፓ ይልቁንም በምሥራቅ አውሮፓ የሚገኙት ናቸው። በእነዚህ አገራት የሴቶች ቁጥር ከወንዶች አንጻር በሰፊ ልዩነት የበለጠው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እንደሆነ በዘገባው የገለጸው ወርልድ አትላስ፣ ለዚህም ኹለተኛው የዓለም ጦርነት፣ ረሀብ፣ ስደት እና መሰሉ ምክንያት ተጠቃሽ ነው ተብሏል።

ዚምባቡዌ ከጠቅላላ ሕዝቧ መካከል በ52.3 በመቶ ሴቶች ሲሆኑ፣ ይህም ከዓለም 13ኛ ከአፍሪካ ደግሞ በአንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።


ቅጽ 4 ቁጥር 202 መስከረም 7 2015

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች