መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናየዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሊያገረሽ ይችላል አለ

የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሊያገረሽ ይችላል አለ

የዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሊያገረሽ እንደሚችል ማስጠንቀቁ ተነግሯል፡፡

ቫይረሱ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ መሆኑን የጠቆሙት የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋ ፕሮግራም ቴክኒካል መሪ ማሪያ ቫን ኬርሆቭ ናቸው። እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ ቫይረሱ ዓለም ላይ ሪፖርት ከሚደረገው ቁጥር በበለጠ ሁኔታ እየተዛመተ ይገኛል።

ቴክኒካል መሪው ተናገሩ በተባለው መሠረት፣ ቫይረሱ ዓለም ላይ ሪፖርት ከሚደረገው ቁጥር በበለጠ ሁኔታ እየተዛመተ እንደሚገኝ ተመላክቷል።በመሆኑም፣ ድርጅቱ በኮቪድ19 ወረርሽኝ ስርጭት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ቢመጣም፣ ዳግም ሊያገረሽ ይችላል ሲል ማሳሰቡ ነው የተሰማው።

ከዓለም የጤና ድርጅት ተገኝቷል በተባለው መረጃ መሠረት ነሐሴ 30/2014 እስከ መስከረም 1/201 ባለው ሳምንት በዓለም ዙሪያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር በ28 በመቶ መቀነሱ ተመላክቷል፡፡

በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ካለፈው ሳምንት አንጻር በ22 በመቶ ቀንሷል መባሉም ተዘግቧል።

ሆኖም ግን ወደፊት የኮሮና ቫይረስ ሊያገረሽ እንደሚችል የተጠቆመ ሲሆን፤ በዚህም አገራት ሊፈጠሩ ለሚችሉ ሁኔታዎች ኹሉ ከወዲሁ ነቅተው በመጠበቅ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም ድርጅቱ አሳስቧል ተብሏል። ድርጅቱ በመግለጫው ወረርሽኙን ለመግታት ይበልጥ መፍጠንና መጠንከር የሚገባን ጊዜ ላይ ነን ሲል አቅጣጫ መስጠቱ ተሰምቷል።


ቅጽ 4 ቁጥር 202 መስከረም 7 2015

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች