መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናከ700 ሚሊዮን ብር በላይ በሙስና የተመዘበረ ገንዘብ መታገዱ ተሰማ

ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ በሙስና የተመዘበረ ገንዘብ መታገዱ ተሰማ

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ በሙስና የተመዘበረ ገንዘብ ማሳገድ መቻሉ ተሰምቷል፡፡

በዚህም ከ88 ሚሊዮን ብር በላይ እና 10 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት እንዲሁም የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና መኖሪያ ቤቶች እንዲመለሱ መደረጉን የፍትሕ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በፍትሕ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አወል ሡልጣን፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለይም ሙስናን ከመከላከል አንፃር የተከናወኑ ተግባራትን አብራርተዋል።በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሙስና የተመዘበረ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ተከታትሎ ማስመለስ መቻሉ ሙስና ከመከላከል አንጻር የተገኘ ውጤት መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በመሆኑም፣ በአሁኑ ወቅትም በክርክር ላይ ያሉ እና ክስ የተመሠረተባቸው የሙስና ወንጀል ጉዳዮች እንዳሉ አወል ጠቁመዋል የተባለ ሲሆን፤ ከዚህ ጋር በተያያዘም ምዝበራ ተፈጽሞባቸዋል ተብለው የተገመቱ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብቶችም እንዲታገዱ መደረጉ ተሰምቷል።

በዚሁ መሠረት 701 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ፤ ከ744 ሚሊዮን ብር በላይ የሼር ገንዘብ እና የ27 ሚሊዮን ብር ቦንድም እንዳይንቀሳቀስ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መታገዱን አወል ተናግረዋል።በተያያዘም ከ41 ሺሕ ካሬ ሜትር በላይ መሬትም ታግዶ በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ላይ መሆኑ ተሰምቷል።

በፍርድ ቤት እየተካሄደ ያለው ክርክር እስኪጠናቀቅ የተመዘበሩ ሃብት እንዳይንቀሳቀሱ የተደረገ ሲሆን፣ ጉዳትና ብልሽት እንዳይደርስባቸውም አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሙስና ተመዝብረዋል ተብለው የተያዙ 364 ተሽከርካሪዎች፣ 155 ቤቶችና 617 የተለያዩ ማሽነሪዎችም በተመሳሳይ ለሦስተኛ ወገን ተላልፈው እንዳይሰጡና እንዳይሸጡ ተደርጓል። ከ88 ሚሊዮን ብር በላይ፣ 10 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬትን ጨምሮ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና መኖሪያ ቤቶች ለመንግሥት ገቢ መደረጋቸውንም አስታውቀዋል።

በሙስና የተመዘበሩ ሀብቶች ላይ የሚደረገው የፍርድ ቤት ክርክር ሲጠናቀቅ መንግሥት እና ሕዝብ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል።


ቅጽ 4 ቁጥር 202 መስከረም 7 2015

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች