መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናየግዙፍ ኦተር ቅሪተ አካል በኦሞ ሸለቆ ተገኘ

የግዙፍ ኦተር ቅሪተ አካል በኦሞ ሸለቆ ተገኘ

ኦተር በመባል የሚታወቀው አነስተኛ የውሻና ድመት ቅልቅል የሚመስልና በውሃ ውስጥ የሚኖር እንስሳ ግዙፍ ቅሪተ አካል በኦሞ ሸለቆ መገኘቱን ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል።

ከረጅም ጊዜ የቁፋሮ ምርምር በኋላ የተገኘው ቅሪተ አካል እጅግ ግዙፍ የሆነና አሁን በዓለማችን ከምትገኘው ዝርያ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ነው ተብሏል። ግኝቱን ይፋ ያደረጉት ተመራማሪዎች ለቅሪተ አካሉ ‹Enhydriodon omoensis› የሚል ሳይንሳዊ ሥያሜ መስጠታቸውን ‹ላይቭ ሳይንስ›ን ዋቢ አድርጎ ስፑትኒክ አስነብቧል።

ግዙፍ ቅሪተ አካሉ የዓመታት ቁፋሮ ውጤት እንደሆነ የተናገሩት ተመራማሪዎቹ፣ በአካባቢው ቀዳሚ ሰዎች መኖር በጀመሩበት ወቅት ግዙፍ ኦተሮች ይኖሩ እንደነበር አመላካች ነው ብለዋል። ከ3.5 እስከ 2.5 ሚሊየን ዓመት በፊት በአካባቢው እነዚሁ ግዙፎቹ የባሕር ጠላቂ እንስሳዎች ይኖሩ እንደነበር አረጋግጠዋል።

በኦሞ ሸለቆ የተገኘው ግዙፍ ቅሪተ አካል ላይ በተካሄደ ጥናት ርዝመታቸው ሦስት ሜትር ገደማ የሚሆኑ ሲሆን፣ የአሁኖቹ ግን ግፋ ቢል ከአንድ ነጥብ 2 ሜትር አይበልጡም ተብሏል። አሁን በዓለም ላይ ያለው የትልቁ ክብደት ከአስራዎቹ ኪሎግራም እንደማይዘል የተናገሩት ተመራማሪዎቹ፣ የቅሪተ አካሉ ግን ከ10 እጥፍ በላይ በመብለጥ ከ150 እስከ 250 ኪሎግራም ይመዝን እንደነበር ገምተዋል።

ጥርሱን በማጥናት ክብደቱን የገመቱ ሲሆን አበላሉንም ለማወቅ ሞክረዋል። በአብዛኛው ውሃ ላይ ጊዜያቸውን እንደሚያሳልፉት እንደዘመነኞቹ ኦተሮች ሳይሆን፣ የቀደመው ግዙፉ ዝርያ በአብዛኛው መሬት የሚኖርና ከውሃም ሆነ ከምድር አድኖ የሚበላ ነበር ብለዋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 202 መስከረም 7 2015

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች