መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜና23 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኀን ተቋማት የሥራ ፈቃድ ተቀበሉ

23 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኀን ተቋማት የሥራ ፈቃድ ተቀበሉ

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚያሰራጩ 46 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኀን ተቋማት መካከል 23ቱ ዛሬ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን የሥራ ፈቃድ ወስደዋል።

‹የሃይማኖት መገናኛ ብዙኀን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር› በሚል መሪ ሐሳብ የተጀመረው የሃይማኖት መገናኛ ብዙኀን ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተጠናቋል። በመርሃግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ 23 የሃይማኖት የመገናኛ ብዙኀን የሥራ ፈቃዳቸውን ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ተቀብለዋል።

ቀሪዎቹ 23 የሃይማኖት መገናኛ ብዙኀን ፈቃድ ለመቀበል በሂደት ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ኢቫንጀሊካል ሚዲያ፣ ጂ.ኤም.ኤም ቴሌቪዥን፣ ሰላም ቴሌቪዥን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ አራራት ቴሌቪዥን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን፣ የበረካ ልጆች ቴሌቪዥንና ሌሎች 17 ጣቢያዎች ናቸው ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ፈቃዳቸውን የተቀበሉት።

ሃይማኖታዊ ሐሳቦች የሚዲያ እድል አግኝተው ለኅብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑና ለችግሮቻችን መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል እሳቤ በመነሳት መንግሥት የሃይማኖት ሚዲያዎችን እውቅና መስጠቱ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

የሃይማኖት መገናኛ ብዙኀን፤ የሰላም ግንባታ ላይ የአብሮነት እሴቶች እንዲጎለብቱ የሚያስችሉ ሥራዎችን በመሥራት ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ መገናኛ ብዙኀኑ የችግር መንስኤ እንዳይሆኑ በጥንቃቄ ሊሠሩ ይገባልም ነው የተባለው።


ቅጽ 4 ቁጥር 200 ነሐሴ 28 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች