መነሻ ኮዱን 07 ያደረገው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ድሬዳዋ እና ሀረር ከተሞች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል። ድርጅቱ የሳፋሪኮም ደንበኞች እርስ በርስ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር በሚያደርጓቸው ጥሪዎች በደቂቃ ሀምሳ ሳንቲም ይከፍላሉ ያለ ሲሆን፣ ለኢንተርኔት ደግሞ በ10 ብር 120 ሜጋ ባይት፣ በ50 ብር 900 ሜጋ ባይት እንዲሁም በ100 ብር ደግሞ ኹለት ጊጋ ባይት መጠን ያለውን ኢንተርኔት ለ30 ቀናት በመደበኛነት በመሸጥ ላይ እገኛለሁ ብሏል። በቀጣዮቹ ስምንት ወራት 25 የሚሆኑ የኢትዮጵያ ከተሞችን የማዳረስ እቅድ እንዳለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል።
ቅጽ 4 ቁጥር 200 ነሐሴ 28 2014