መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየኢትዮ-ቱርክ የኢንቨስትመንት ፎረም በቱርክ ተካሄደ

የኢትዮ-ቱርክ የኢንቨስትመንት ፎረም በቱርክ ተካሄደ

አርብ ግንቦት 19 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከአዳና ቻምበር ኦፍ ፎረም እና ከአዳና ቆንስላ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት እድል የሚያስተዋውቅ ፎረም በቱርክ አዳና ከተማ ተካሂዷል።

በፎረሙ በቱርክ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ባለሃብቶች እንዲሁም የሦስት ከተሞች የክብር ቆንስላዎች ተሳትፈዋል።

የአዳና ከተማ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቲላ ሜኔቭስ መሰል ፎረም ከኤምባሲው ጋር በጋራ መዘጋጀቱ በኹለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነትን የበለጠ ለማሳደግ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

በአዳና የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ዩሱፍ ካን፤ በኹለቱ አገሮች መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ኹኔታ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሀመድ ባደረጉት ንግግር፥ የኹለቱ አገራት መሪዎች በኢንቨስትመንት፣ በንግድና በፖለቲካ ዘርፎች በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን በመግለጽ ሥምምነቶቹን ወደ ተግባር ለመቀየር በትብብር መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ምቹ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ለቱርክ ባለሃብቶች ጥሪ አቅርበዋል።

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ኔሜ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ኹኔታ፣ ስለተደረጉ የኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች፣ የትኩረት መስኮች ፣ ያሉ ማበረታቻዎች እና እድሎች አስረድተዋል::

በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ለሚፈልጉ የቱርክ ባለሀብቶች ኹሉ ፅ/ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ከአንካራ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች