መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናበኦሮሚያ ክልል 'ቡሳ ጎኖፋ' የተሰኘ ንቅናቄ ተጀመረ

በኦሮሚያ ክልል ‘ቡሳ ጎኖፋ’ የተሰኘ ንቅናቄ ተጀመረ

ዕረቡ ግንቦት 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል የገዳ ሥርዓት አካልና የኦሮሞ ሕዝብ ጥንታዊ የመረዳጃ ሥርዓት ነው ተባለ ”ቡሳ ጎኖፋ” ንቅናቄ ተጀመረ።

ሥርዓቱ የኦሮሞ ሕዝብ ሰው ሰራሽም ይሁን ተፈጥሯዊ ችግር ሲያጋጥመው ችግሩን ለማለፍ የሚታገዝበት ጥንታዊ ባህል ነው ተብሏል።

ንቅናቄውን ማስጀመር ያስፈለገበት ምክንያትም፤ የሕዝቡን የመረዳዳት ባህል ለማጎልበት እንደሆነና የክልሉ መንግሥት ሥርዓቱ ተቋማዊ መልክ እንዲኖረው ቢሮ ተደራጅቶ እየተመራ መሆኑ ታውቋል።

በንቅናቄው ማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራልና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች