በኢትዮጵያ የናሚቢያ ኤምባሲ ሠራተኞች ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ቅዳሜ፣ ግንቦት 10 በታጠቁ ዘራፊዎች መዘረፉን አስታወቁ። በባልደረቦቹ ላይም ምንም ዓይነት የአካል ጉዳት አለመድረሱን የተናገረው ኤምባሲው ገንዘብ፣ ጌጣጌጥ፣ የሞባይል ስልኮች እና ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ከተዘረፉት ንብረቶች መካከል መሆናቸውንም ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ለአዲስ አበባ ፖሊስ ካራማራ ፖሊስ ጣቢያ የደረሰውን ዘረፋ ያመለከተው ኤምባሲው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲፕሎማቶች ላይ እየተደጋገመ የመጣው ይህ ዘረፋ እንዳሳሰበውም ገለጿል። በአፍሪካ ኅብረት የናሚቢያ ልዩ መልክተኛ እና በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን በአፍሪካ እንዲሁም የአገሪቱ አምባሳደርም ድርጊቱ በጥልቀት እንዲመረመር እና በአጠቃላይም በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ላይ እየተፈጠረ የሚገኘው ሥጋት መንግሥት እንዲስወግድለት ጠቅሷል።
ቅጽ 1 ቁጥር 29 ግንቦት 17 2011