መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየመኖርያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ተራዘመ

የመኖርያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ተራዘመ

አርብ መጋቢት 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኖርያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ ያወጣውን ደንብ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ማራዘሙን አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖርያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱን አስታውሷል።

ደንቡ ላለፉት ሦስት ወራት እንዲራዘም ተደርጎ እንደነበረም ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት እንዲራዘም መወሰኑን አሳውቋል።

በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

” ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብና የመተጋገዝ ባህላችንን በማሳደግ ፈታኝ ሁኔታዎች በጋራ ሆነን እንሻገር ” ሲልም የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አስተላልፏል።
________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች