የአዲስ አበባ ፖሊስ ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ የጦር መሳሪያዎችንና የገንዘብ ኖቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ

0
524

ሐሙስ መጋቢት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኮማንደር ፋሲካ አሰፋ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ በተሠራው ሥራ ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ በአይነት የሚለያዩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችንና የገንዘብ ኖቶችን በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

በከተማዋ በተደረገ ፍተሻና ብርበራም 47 ቦምብ፣ 8 ፈንጂዎች፣ 113 ክላሽን ኮቭ ጠብመንጃ፣ 422 ልዩ ልዩ ሽጉጦች ከ17 ሺህ በላይ የክላሽን፣ ከ8ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይቶች፣ 2ሺህ 901 የብሬን፣ 8 የመትረየስ እና 183 የልዩ ልዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶች መያዝ ተችሏል ብለዋል ኮማንደር ፋሲካ።

ከእነዚህ የጦር መሳሪያዎች በተጫማሪ 57 የጦር መሳሪያ መነፅር፣ 2 የጦር መሳሪያ ኮምፓስ፣ 64 ወታደራዊ የመገናኛ ሬድዮ፣ 3 የመገናኛ ሬዲዩ ቻርጀር፣ 6 ጂፒኤስ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁስ ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተይዘው አስፈላጊው ምርመራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዘውውርን ለመከላከል ሕገወጦችን ሕግ ፊት የማቅረቡ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል።
ከሐምሌ 30/2014 እስከ ታኅሣሥ 30/2014 ባለው ጊዜ በከተማው ልዩ ልዩ ሥፍራዎች 18 ፈንጂዎች፣ 50 ቦምብ፣ 1ሺህ 544 የብሬን እና የዲሽቃ ጥይቶች፣ 21 ክላሽን ኮቭ ጠብመንጃዎች፣ 16 ሽጉጦች፣ 20 የመገናኛ ሬዲዮኖች፣ 11 የጦር ሜዳ መነፅር፣ ከ2ሺህ በላይ ልዩ ልዩ የፀጥታ አካላት የደንብ ልብሶች እና ሌሎች ቁሳቁስ ተጥለው ተገኝተዋል መባሉን አሚኮ ዘግቧል።

ኮሚሽኑ በከተማዋ ካሉ የተለያዩ የሰላምና ደኅንነት ተቋማት ጋር በጥምረት እየሠራ መሆኑንም አስታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here