መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ማቅረቢያ ዛሬ ይጠናቀቃል

የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ማቅረቢያ ዛሬ ይጠናቀቃል

አርብ ጥር 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ዛሬ ጥር 13 ቀን 2014 እንደሚጠናቀቅ ጥቆማ ተቀባይ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸውና የአገራችንን ህልውና የሚፈታተኑ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ ለመጪው ትውልድ ሰላማዊ አገር ለማስረከብ የሚያግዝና ከሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለልተኛ የሆነ ኮሚሽን እንደሚቋቋም ይታወቃል፡፡

ይህንን ኮሚሽን የሚመሩት ኮሚሽነሮች በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥቆማ ተቀባይነት ከታህሳስ 26 ቀን 2014 እስከ ጥር 13 ቀን 2014 ድረስ ህዝቡ በተለያዩ አማራጮች ጥቆማ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ዛሬ ጥር 13/2ዐ14 የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ የመጨረሻ ቀን በመሆኑ እስካሁን ጥቆማ መስጠት ያልቻሉ አካላት ዛሬ ጥር 13/2014 ጥቆማ መስጠት የሚችሉ መሆኑን የጥቆማ ተቀባይ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

“እንደ ዜጋ በአገራዊ ጉዳይ ላይ የመወሰን መብትን በመጠቀም ጥቆማውን እንድታደርጉ” በማለት በም/ቤቱ የተቋቋመው የጥቆማ ተቀባይ ኮሚቴ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
_______________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች